ስለ የባህል ዕቅዱ:
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰለሳ-ዓመት አጠቃላይ ዕቅድ፣ የሞንትጎመሪ ማበብ 2050፣ የጸደቀው ኦክቶበር 2022 ዓ.ም ላይ ሲሆን፣ ለካውንቲው አዲስ የባህል ዕቅድ እንዲወጣ ያመላክታል። ከ 2 ዓመት በላይ መረጃዎች ከተሰበሰቡ እና አዲስ ዕቅድ እንዲወጣ መሠረቱ ከተደላደለ በኋላ፣ AHCMC የባህል ዕቅድ ማውጣት ሂደቱን እንዲመራ 2024 ዓ.ም ላይ ሜትሪስ አርትስ ኮንሰልቲንግን መርጧል።
በቀጣዮቹ 17 ወራት ጊዜ ውስጥ ተዘጋጅቶ፣ የስነ ጥበብ እና የሰብዓዊነት ተግባራትን፣ የስነ ጥበብ እና የሰብዓዊነት ድርጅቶችን፣ እና በመላው ሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የሚገኙ የባህል ተቋማትን ለመደገፍ እና ለስነ ጥበብ እና ባህል እያንዳንዱ ነዋሪ ምክንያታዊ የሆነ ተደራሽነት እንዲኖረው ለማረጋገጥ ለካውንቲው እና ለመምሪያዎቹ አዲሱ የባህል ዕቅድ መዋቅር ይፈጥራል።
ስለ አማካሪዎቹ፦
ሜትሪስ አርትስ ኮንሰልቲንግ ተልዕኮው የባህል ህያውነትን ማሻሻል እና መለካት ሲሆን የምርምራ እና የዕቅድ አውጪ አማካሪ ድርጅት ነው። ሜትሪስ ባህል የሰዎችን ሕይወት ማበልጸግ ላይ ኋይል እንዳለው፣ ማህበረሰቦች እንዲያብቡ እንደሚረዳ፣ ማህበረሰቦችን እንደሚያጠናክር እና አባልነትን ማነሳሳት እንደሚችል ያምናል። በፈጠራ የተሞላ ቦታ የመፍጠር አለም ውስጥ ያለው ስራ ተግባሩን እንዲፈጽም አነሳስቶታል። 2010 ዓ.ም ላይ ለናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዘ አርትስ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚቀርበውን ሪፖርት የእኛ መስራች በጋራ ደርሷል። ሜትሪስ ለማህበረሰብ ዕድገት ስነ ጥበባት እና ባህል ወሳኝ መሳሪያ ሊሆኑ እንደሚችሉ መለየት ላይ ዋና ተሟጋች እንደሆነ ይቀጥላል። ወሳኝ የሆኑ አገልግሎቶችን ይሰጣል እነዚህም- የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ማህበረሰብ እና የስነጥበባት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የሚጨምሩ በመላው ካውንቲ ውስጥ ለሚገኙ ደንበኞች የማቀድ፣ ፕሮግራም ማውጣት፣ ግምገማ፣ እና ለመስክ ግንባታ ጥናት ማድረግ ናቸው።
የባህል ዕቅድ ማውጣት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችን የሚለይ፣ መዋዕለ ንዋዮችን የሚመራ፣ ስለ ስነጥበብ እና ባህል በተመለከተ ለአካባቢው ፖሊሲዎች ማሳወቅ ስራ የሚሰሩ በቦታ ላይ የተመሰረቱ ዕቅዶችን የመፍጠር ተግባር ነው። የባህል ዕቅዶች አንድ አካባቢ (በዚህ ጉዳይ ላይ ሞንትጎመሪ ካውንቲ) የሚከተሉትን እንዴት እንደሚያከናውን እገዛ ይሰጣሉ፦
- የመንግስት እና የግል ዘርፍ ገንዘቦችን መጠቀም
- ተቋማትን መገንባት
- ደንቦችን ማውጣት ወይም መቀየር
- የህዝብ ቦታዎችን እና የመንግስት ህንፃዎችን መጠቀም
- የኢኮኖሚ ልማት እና ቱሪዝምን ማበረታታት
- የትምህርት ወይም የስነ ጥበብ ፕሮግራሞችን መደገፍ
- በካውንቲው ውስጥ ስነ ጥበባትን እና ባህልን የሚነኩ ሌሎች ውሳኔዎችን መወሰን
እንደዚህ ያሉ ጉዳዮች ላይ ካውንቲው እንዴት እንደሚወስን በመግራት፣ የባህል ዕቅዶች በተጨማሪም የካውንቲውን የገንዘብ ምንጭ እና ፖሊሲ ውሳኔዎች ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። ለሁሉም ነዋሪዎች የስነጥበባት እና የባህል ፕሮግራሞች ላይ ፍትሃዊ የሆነ ተደራሽነት እንዲኖር ያበረታታል። የመኖሪያ ቤት፣ የኢኮኖሚ ልማት፣ የጤና እና የትምህርት ጉዳዮች ላይ ካውንቲው የሚያደርገው ጥረት ላይ ፈጠራን በማከል እና አዳዲስ አመለካከትን በማምጣት ባህላዊ ባልሆነ መንገድ የመንግስት ስራ ላይ እንዴት ስነ ጥበባት፣ ባህል እና ሰብዓዊነት ሊዛመዱ እንደሚችሉ ፍኖተ ካርታዎችን ያወጣል። የባህል ዕቅዶች፣ ልክ እንደ የኦክላንድ ሰው መሆን፦ የባህል ልማት ዕቅድ በተጨማሪም በአካባቢው የሚገኙ ቦታዎች የባህል እና የዘር ፍትሃዊነትን እንዲያሳድጉ እና የጸረ-ዘረኝነትን ፖሊሲዎች ማራመድ እንዲችሉ መሰረቱን ይገነባል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመጨረሻው የባህል ዕቅድ የወጣው 2002 ዓ.ም ላይ ነበር። ከዚያን ጊዜ አንስቶ፦
- ሞንትጎመሪ ካውንቲ በፍጥነት አድጓል እና በጣም ብዝሀነትን ጨምሯል። ከ 2000 እስከ 2020 ዓመት ድረስ የካውንቲው የህዝብ ቁጥር መጠን 20 በመቶ ጨምሯል። በተጨማሪም፣ በዚህ ተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ የካውንቲው ነጭ ያልሆኑ ነዋሪዎች ቁጥር በ 80 በመቶ ጨምሯል። በአሁኑ ሰዓት በግምት 60 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ነጭ ያልሆነ ነው።
- ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁላችንም ላይ ተጽእኖ አሳድሯል፣ ከወረርሽኙ እና ከስራ መዘጋቱ ድረስ ያለው ሰፊው የምጣኔ ሀብት እና የማህበራዊ ለውጦች በተጨማሪ፣ አርቲስቶች እና ስነ ጥበቦች እና የባህል ድርጅቶች የገቢ ማጣት ሁኔታ ታይቶባቸዋል እና ፕሮጀክታቸውን እና ፕሮግራማቸውን እንዴት እንደሚያስቀጥሉ እና ደንበኞቻቸውን እና ማህበረሰቦቻቸውን እንደሚያገልግሉ ለውጦችን ለማድረግ ተገደዋል።
- የእኛ ተልዕኮዎች እና እሴቶች እየተሻሻሉ መጥተዋል። ሁለቱም AHCMC እና ካውንቲ ካውንስሉ የገንዘብ ማውጣት፣ ፕሮግራም መቅረጽ እና ውሳኔ መስጠት ላይ የዘር ፍትሃዊነትን ለማስረጽ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
- የባህል ዕቅድ ማውጣት ሥነምግባር በራሱ ለውጥ አሳይቷል። የተለመደው የባህል ዕቅድ ማውጣት ስራ አርቲስቶችን እና የባህል ተቋማትን ማገልገል እና ከስነ ጥበቦች እና ከባህል እንቅስቃሴዎች ላይ የሥነ ምጣኔ ጥቅሞችን ማግኘት ላይ ያተኩራል። እነዚህ አስተሳሰቦች አሁንም ቢሆን ለጥረቱ ማዕከላዊ በመሆን ያገለግላሉ፣ ነገር ግን የባህል ዕቅድ ትኩረት ዛሬ በጣም ሰፊ ነው። ዘመናዊ የባህል ዕቅድ ማውጣት ሂደት ስነ ጥበብ እና ባህል እንዴት እንደሚቆራኙ እና የካውንቲውን ሌላኛውን ስራ እና ልክ እንደ መኖሪያ ቤት፣ ጤና፣ እና ደህንነት እና የማህበረሰብ ግንባታ የመሳሰሉ፣ ወሳኝ የነዋሪዎችን ህይወት ገጽታዎችን ሊያራምዱ ይችላሉ።
- ካውንቲው ስነ ጥበብ እና ባህል ላይ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ ያለ ሲሆን ይሄም ዊተን አርትስ ኤንድ ካልቸራል ሴንተር ዕቅድ ማውጣት ያካትታል። ይሄ ፕሮጀክት ስነ ጥበብ እና ባህል ላይ ከካውንቲው በተለምዶ ድጋፍ ላላገኙ ማህበረሰቦች እና ድርጅቶች መዋዕለ ንዋይ ድጋፍ ለመስጠት ዕድሉን ይከፍታል።
ስነ ጥበብ እና ባህል የእኛ ራስን የመግለጽ፣ ጤናችንን ለማህበረሰባችን እና እርስ በእርስ አባላት መሆናቸንን ወሳኝ አካል መሆናቸውን እንገነዘባለን። ስነ ጥበቡ የሁሉም ሰው እንደሆነ እና እያንዳንዱ ቀን ላይ ባህል ደግሞ በዙሪያችን አለ። ለካውንቲው አዲስ የባህል ዕቅድ የማውጣት ሂደት ላይ፣ ለሁሉም ነዋሪዎች የስነ ጥበብ እና የባህል ተሞክሮ እና ራስን የመግለጽ ተደራሽነት የሚያሳድግ መዋቅር ውስጥ የእኛን የዘመኑ ዕውቀቶች፣ መርሆች፣ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችን በጋራ ማቀናጀት እንችላለን።
የስነ ጥበብ እና ባህል የእኛን አረዳድ ያሳፋል
- ባህላቸውን የማስቀጠያ ዘዴ፣ ሕይወታቸውን መኖር፣ እና በግል ራሳቸውን መግለጽ ላይ የፈጠራ እንቅስቃሴዎች ላይ ሰዎች የሚሳተፉበትን ታሪካዊ፣ የዘልማድ እና የሚደሰቱበትን መንገድ መረዳት።
- ለሁሉም የማህበረሰብ አካላቶች ግብዓቶች እንደቀረቡ ማረጋገጥ፣ በተለይ ከታሪክ አንፃር ግብዓቶችን ባነሰ መልኩ የሚያገኙትን የባህል ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ ማስቻል።
- በአረዳድ እና በችግር መፍታት መሰረት በማህበረሰቦች እና ባህሎች መካከል ያለውን ክፍተት መሙላት።
- ስነጥበብ እና ሰብዓዊነትን በመጠቀም ልክ እንደ ፍትሃዊነት፣ የማህበራዊ ፍትህ፣ እና ዘላቂነት ለመሳሰሉ ሰፊ ዓላማዎች ግብዓቶችን መጠቀም
ከካውንቲው መንግስት ጋር የስነጥበብ እና ባህል ዝምድናን ማስፋፋት
- ለሞንትጎመሪ ካውንቲ መንግስት ሁሉንም የሚሸፍን የባህል ፖሊሲ መፍጠር
- የካውንቲውን ግብዓቶች በመላው ኤጀንሲዎቹ ውስጥ ማዛመድ — ይሄም የገንዘብ ፈንዱን፣ ተቋማት እና መሬት፣ የፕሮግራም ማውጣት እና የትምህርት እንቅስቃሴዎች፣ የማህበረሰብ ዕቅድ አስተዳደሩ እና የመሬት ልማቱን- ከባህል ፖሊሲው ጋር ማዛመድ ናቸው።
- በ ማበብe 2050 ላይ የስነ ጥበብ፣ ባህል እና ማህበረሰብ ጥቆማዎችን መገንባት።
- የካውንቲው ኢኒሼቲቮች ላይ የሰዎችን የራሳቸውን፣ የማህበረሰባቸውን እና የባህላቸውን እውቅና ማሳደግ።
- የካውንቲውን የፈጠራ እና የብዝሃነት ላይ የመጋቢነትን መንፈስ መፍጠር
አዲስ የሚለመድ ነገር መፍጠር እና መገንባት
- ከወረርሽኝ ጋር በተያያዘ፣ የሥነ ምጣኔ እና የፖለቲካ መረጋጋት ሁኔታ ላይ ስነ ትበብ፣ ባጅል እና የሰብዓዊነት ዘርፎችን ማረጋጋትን ማስቀጠል፣ አቅምን ለመደገፍ የሚያስፈልጉትን አዲስ የመረጋጋት መለኪያዎችን እና ግብዓቶችን መለየት፣ የተልዕኮ ስኬትን ማሳለጥ፣ እና አዲስ ዕድሎችን መከተል
- ስነ ጥበብ፣ ሰብዓዊነት፣ እና የባህል እንቅስቃሴዎች ላይ የገንዘብ ተደራሽነት እና ማቅረብ ላይ ያሉ ኢፍትሃዊነቶችን ለመፍታት መቀጠል
- የስነ ጥበብ ድርጅቶች እና በሰፊው ማህበረሰብ መካከል የስነጥበብ እና የባህል አካታችነት ላይ የጋራ ራዕይ ማስቀመጥ
- ለስነጥበብ እና ለባህል የሚመደቡ የካውንቲው ግብዓቶች ከካውንቲው ህዝብ ቁጥር መጠን እና የብዝሃነት ማህበረሰቦችን እየጨመረ የመጣ ፍላጎቶች ጋር እንዲጣጣሙ ማድረግ
ትክከለኛ መንገዶችን መለየት
- የጋራ ግባችንን እና የባህል ዕቅድ ውስጥ የሚሰጡ ምክሮችን ለማሳካት ለAHCMC፣ ለካውንቲው ኤጀንሲዎች እና ለስነጥበብ፣ ባህል፣ ለሰብዓዊነት ድርጅቶች የተነጠሉ ሊተገበሩ የሚችሉ እርምጃዎችን ማቅረብ
- በስነጥበብ፣ ባህል እና የሰብዓዊነት ስርዓት ምህዳር ውስጥ ያሉ የአቅም ወይም የመዋቅር ክፍተቶችን ለመፍታት አዲስ ፖሊሲ፣ የክዋኔ፣ የድርጅታዊ፣ ወይም የመዋቅር ቅንብሮች መጠቆም
ፍትሃዊ የልማት ተግባራቶችን እና በማህበረሰቡ ላይ የተመሰረቱ የስነ ጥበብ እና ባህል ለማንጸባረቅ ለተንኳሻዊ ፕሮጀክቶች ዕድሎችን እና የአጋርነት ሁኔታዎችን መለየት
የካውንቲውን የባህል ዕቅድ ማውጣት ሂደትን እንዲመራ AHCMC ከ ሜትሪስ አርትስ ኮንሰልቲንግ ጋር በጋራ ይሰራል። ሜትሪስ ስራውን የጀመረው ሴፕቴምበር 2024 ሲሆን ለነዋሪዎች፣ ስነ ጥበበኞች እና የባህል ተሸካሚዎች፣ ለስነጥበብ እና የባህል ድርጅቶች፣ ለካውንቲ መንግስት ኤጀንሲዎች፣ እና ሌሎች ጠቃሚ ድምጾች የመድረስ ተግባራትን ይፈጽማል። ሜትሪስ በመላው 2025 ዓ.ም ላይ የተሳትፎ እና የዕውቀት መሰብሰብ እንቅስቃሴዎችን ይፈጽማል እና በሰበሰቡት የብዝሃነት የማህበረሰብ ግብዓቶች በኩል የሚቃኙ ፍትሃዊ፣ አካታች እና መጪውን የሚያዩ ዕቅዶችን ይፈጥራል ዕቅድ በካውንቲው ካውንስል እና በAHCMC ቦርድ 2025 ዓ.ም መጨረሻ ላይ እንዲተገበር ዕቅዱን ለማቅረብ እንፈልጋለን። የAHCMC ሰራተኞች እና ቦርዱ፣ ከተለያዩ የካውንቲው መመሪያ የተውጣጡ የአማካሪ ኮሚቴ፣ እና የሰፊው ማህበረሰብ አማካሪ ቡድኖች የዕቅድ ማውጣት ሂደቱ ላይ ከሜትሪስ ጋር በጋራ ይሰራሉ።
ሂደቱ ሲቀጥል ጊዜ የተሳትፎ ዕድሎች ማግኘት ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይሄንን ድረገጽ ይጎብኙ።