Cultural Plan in Amharic | የባህል ዕቅድ በአማርኛ

Click for English Haga clic para español 点击查看中文 Dịch sang tiếng Việt           Cliquez pour le français 한국어를 보려면 클릭하세요 

ለመሳተፍ ዝግጅቶች እና ዕድሎች 

የባህል ዕቅድ መጀመር

እሮብ ኦክቶበር 16 ቀን፣ 2024 ዓ.ም ላይ፣ AHCMC የባህል ዕቅድ ሂደትን ለማስጀመር በስትራትሞር ሙዚቃ አድራሻ ውስጥ 125 ድጎማ ሰጪዎች፣ አጋሮች እና ድጋፍ ሰጪዎች ተሰብሰበው ነበር። የእኛን የባህል ዕቅድ አማካሪ ቡድን፣ ሜትሪስ አርትስ አማካሪ ድርጅት [Metris Arts Consulting] በማስተዋወቅ ለአዲሱ ዕቅድ የእኛን ግቦች ላይ ተወያይተናል። ዝግጁቱ የኦክላንድ ከተማ የባህል ጉዳዮች አስተዳዳሪ የሆኑት ሮቤርቶ ቤዶያ የመክፈቻ ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዞ ነበር። ቤዶያ “የኦክላንድ ባለቤትነት የባህል ልማት ዕቅድ” የሚለውን የኦክላንድ የባህል ዕቅድ አፈጣጠር ላይ ስለሰሩት ሥራ ለታዳሚዎች ተናግረዋል። ፍትሃዊነት የዕቅዱ አንቀሳቃሽ ሃይል ነው፣ ባህል ክፈፉ ሲሆን ባለቤትነት ደግሞ ግቡ ነው ብለዋል። የስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ፣ ቀለምማ የወረቀት አይሮፕላኖች ላይ ተሳታፊዎች ምኞታቸውን በመፃፍ በአየር ላይ በማንሳፈፍ ልከዋል። ምኞታቸው የብዝሐነት እና የባለቤትነት እሴቶችን አስተጋብቷል፣ ከእነዚህም መካከል “የማያውቁትን የሚታወቅ ማድረግ፣ የተለያየ አስተዳደግ ያላቸውን ማህበረሰቦች ማገናኘት እና አዲስ ነገር ማወቅን ማበረታት” እና “ሁላችንም ባለቤት እንድንሆን፣ እንድንቆይ፣ እንድንሳፈፍ!” የሚሉት ናቸው። የፎቶ ጋለሪ | ተንሸራታች ዴክ

የወጣቶች ከተማ አዳራሽ

ከምክር ቤት ዓባል ናታሊ ፋኒ-ጎንዛሌዝ ቢሮ ጋር በመተባበር፣ የእኛ ወጣት ነዋሪዎችን ልዩ ዝንባሌዎች፣ ፍላጎቶች፣ እና ሐሳቦች ግንዛቤ ለማግኘት በዊተን የወጣቶች ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ማርች 31፣ 2025 ዓ.ም ላይ ስብሰባ አካሂደናል። በመካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች ክፍት የሆነው የከተማው ማዘጋጃ ቤት ለተማሪዎችን የባህል እቅድን በማስተዋወቅ በማህበረሰባቸው ውስጥ እያጋጠሙ ስላሉ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ አስተያየታቸውን እንዲሰጡን እና ጥበብ፣ ባህል እና የፈጠራ አገላለጽ እነዚህን ችግሮች መፍታት ላይ እንዴት እንደሚረዳን ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። አጀንዳው ተለዋዋጭ እና የፈጠራ እንቅስቃሴዎችን፣ የተመራ የቡድን ውይይቶችን እና በግራፊክ ማስታወሻ ጸሐፊ እና በአካባቢው ወጣቶች ዘጋቢዎች የተቀረጸ ነበር። ዝግጅቱ የተካሄደው የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች በተዘጉበት ቀን ላይ ነው። ተማሪዎች በመገኘታቸው የማህበረሰብ አገልግሎት ሰዓትን አግኝተዋል። ቪዲዮዎች፦ ማጠቃለያዎች፣ የማህበረሰብ ግጥም፣ ሙሉ | ፎቶ ጋላሪ | ተንሸራታች ዴክ

የባህል ጥበቃዎች ብቅ-ባዮች

የባህል ጥበቃዎች የሚባሉ የአርቲስት ብቅ ባይ ዝግጅቶችን በመጠቀም በመላው ካውንቲ ውስጥ ነዋሪዎች ጋር እንደርሳለን። የአካባቢው አርቲስት ሆሊ ባዝ የነደፈው ይህንን የፈጠራ የማህበረሰብ ተሳትፎ ፕሮጀክት ሲሆን በመንገድ ላይ ያሉ ሰዎች ለአስተሳሰብ ጥያቄዎች ምላሾችን እንዲያበረክቱ እና በሜሶን ማሰሮ ውስጥ እና በፎቶግራፍ “የተጠበቁ” በሚያምር ወረቀት ላይ እንዲመዘገቡ ይጋበዛሉ። እንደ “ይህን ማህበረሰብ ለእርስዎ ቤት የሚያደርገው ነገር ምንድን ነው?”ያሉ ጥያቄዎች የሰዎች ምላሾች በእቅድ ሂደቱ ውስጥ እንደ “ባለቤትነት” የመሳሰሉ የምንመራመርባቸው ጭብጦች ላይ አዲስ እይታን ይሰጣሉ። እንደ የገበሬዎች ገበያ ማዕከል፣ የባህል እና የሃይማኖት በዓላት፣ እና የምግብ ማከፋፈያ ማዕከላት የመሳሰሉ የመሰብሰቢያ ቦታዎች ውስጥ ብቅ በማለት በሰባቱ የካውንቲው ካውንስል ዲስትሪክቶች ውስጥ የባህል ጥበቃ ዝግጅቶችን እናዘጋጃለን። 

የባህል ጥበቃዎች እዚህ ላይ ያግኙ፦ 

የተረጋጋጠ 

      ጊዜያዊ 

          የፎቶ ጋለሪ 

          የማህበረሰብ የዳሰሳ ጥናት

          በተቻለ መጠን ከበርካታ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎች አስተያየቶችን ለመሰብሰብ፣ በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚቀርብ የዳሰሳ ጥናት ለህዝቡ እያዘጋጀን ነው።  የዳሰሳ ጥናቱ ጥያቄዎች በመላው ካውንቲ ውስጥ ከሚገኙ ነዋሪዎች የተለያዩ አመለካከቶችን ለመረዳት የተዘጋጁ ናቸው።  ስለዚህ የዳሰሳ ጥናቱ በካውንቲው ውስጥ ተዘውትረው በሚነገሩ ቋንቋዎች ማለትም እንግሊዘኛ፣ ስፓኒሽኛ፣ አማርኛ፣ ቻይንኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ኮሪያኛ፣ እና በቬትናምኛ ይነገራሉ።  የዳሰሳ ጥናቱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ኪነ ጥበብ፣ ባህል፣ እና ቅርስ ላይ ነዋሪያዎች ቅድሚያ የሚሰጡትን ነገር ይጠይቃል።   በተጨማሪም ለግለሰብ አርቲስቶች፣ ለፈጠራ ዘርፍ ንግድ ተቋማት፣ እና ኪነ ጥበቦች፣ ባህል፣ እና የሰብዓዊነት ድርጅቶች ጥያቄዎችን ይዟል። 

          የዳሰሳ ጥናቱ ላይ ይሳተፉ። 

          የማህበረሰብ ውይይቶች

          በተቻለን መጠን ከበርካታ የማህበረሰቡ ዓባላት ስለ ፍላጎታቸው እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ኪነ ጥበብ፣ ባህል፣ እና ቅርስ ጉዳይ ላይ ቅድሚ ስለሚሰጡት ነገር ለማወቅ እንፈልጋለን።  “በሳጥን ውስጥ መሰብሰብ” የሚባል ልዩ ዘዴን በመጠቀም፣ የራሳቸውን የማህበረሰብ ውይይቶች መምራት እንዲችሉ ዝንባሌው ያላቸውን የባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ መሣሪያ ጥቅል አዘጋጅተናል።  በመቀጠል ለዕቅዱ ግብዓት ለመስጠት የእነሱን ግኝት ከእኛ ጋር ማጋራት ይችላል። ልክ እንደ ሁሉም ሰው ባለቤትነት ስሜት የሚሰማው እና የበለጸገ ሕይወት እንዲመሩ የሚያስችሉ ማህበረሰብ መፍጠር፣ አርቲስቶቻችንን እና የእኛን የባህል ማህበረሰቦችን ማበልጸግ፣ እና የማህበረሰብ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲያግዙ ኪነ ጥበባት፣ ባህል፣ እና ሰብዓዊነቶችን መጠቀም የመሳሰሉ ርእሶች ላይ ለመወያየት የሚያስችሉ ስኬታማ ስብሰባዎች ላይ እንዲሳተፍ አዘጋጆችን በማዘጋጀት የማሰልጠን ሥራን እንሰራለን። በባህላዊ የተሳትፎ መንገዶች ላይ ሊገኙ የማይችሉ ከፍተኛ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ባለድርሻ አካላት (ከኤልሳልቫዶሪያን ነዋሪዎች እስከ ቤተ-መጻሕፍት!) ግንኙነት ያላቸውን አስተናጋጆች እየቀጠርን ነው። የማህበረሰብ ውይይት ስልጠና እና የመሳሪያ ጥቅል ስብሰባ ለማካሄድ ለሚፈልግ ለማንኛውም ሰው ክፍት ነው። 

          የራስዎን የማህበረሰብ ውይይት የመሣሪያ ጥቅል/አዘጋጅ ይጠይቁ 

          ለቦርዱ እና ለመማሪያ ክፍሎች ማቅረብ

          በመላው ካውንቲ ውስጥ ለሚኖሩ በርጃታ ቡድኖች አጭር የማብራሪያ ዝግጅት በማድረግ ስለ የባህል ዕቅድ ሂደት ንቃትን እናስፋፋለን። በእነዚህ በምናቀርባቸው ዝግጅቶች፣ ከሰዎች እና ቦርድ ከሚወክላቸው ንግድ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመፍጠር የዕቅድ ማውጣት ሂደቱ ላይ የተሳታፊዎችን ቁጥር እንደምናሳድግ ተስፋ እናደርጋለን። በተጨማሪም፣ ልክ እንደ የእርሻ ማከማቻ የመሳሰሉ የካውንቲው ሰፊ ቦታዎች ላይ በርካታ የኪነጥበብ ወይም የሲቪክ ትምህርቶችን እንጎበኛለን።  በዚህ መንገድ፣ በዊተን ውስጥ የሚገኘው የወጣቶች መዘጋጃ ቤት አዳራሽ ላይ መሳተፍ ከማይችሉ ወጣቶች አስተያየቶችን ማግኘት እንችላን።  ዕቅዱን፣ በአካል/ወይም በርቀት ለማቅረብ አቅደናል፦ 

          • የከተማ አጋርነት ቦርዶች
          • የኪነጥበባት እና የመዝናኛ ዲስትሪክት ቦርዶች 
          • የሞንትጎመሪ ካውንቲ ቻምበር ኦፍ ኮሜርስ 
          • የሞንትጎመሪ ካውንቲ አፕሮፕሬሽን ኮሚቴ  
          • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኢኮኖሚ ልማት ትብብርን ይጎብኙ 
          • የሞንትጎመሪ ካውንቲ ዕቅድ አውጪ፣ የሜሪላንድ-ብሔራዊ ካፒታል ፓርኮች እና የዕቅድ ማውጣት ኮሚሽን 
          • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች 
                        የባህል ዘርፍ የትኩረት ቡድኖች

                        ወሳኝ የባህል ዘርፍ/የፈጠራ ኢኮኖሚ ባለድርሻ አካላት ላይ ለመድረስ፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ የሚኖሩ እና የሚሰሩ የፈጠራ ባለሙያዎች ጋር በአካል የሚደረግ የትኩረት ቡድኖች ላይ ተከታታይ ይይቶችን እናደርጋለን። የመፍጠር ተሞክሮ፣ የማቆየት እና ከሥራዎች እንዴት ገቢ እንደሚያገኙ ጥያቄዎችን እንጠይቃቸዋለን። በተጨማሪም ለካውንቲው ነዋሪዎች እንዴት ኪነጥበብ፣ ባህል እና ሰብዓዊነት ሥራዎችን እንደሚያቀርቡ እንዲሁም ከካውንቲው ሥራ ጋር የእነሱ የፈጠራ ሥራዎች እንዴት እንደሚቆራኝ እንጠይቃቸዋለን። ስድስት አነስተኛ ቡድን ውይይቶችን እናካሂዳለን፣ ለሚከተሉት ለእያንዳንዳቸው አንድ ቡድን፦  

                        • አርቲስቶች፣ የፈጠራ/የባህል ከዋኞች ወይም ተመራማሪዎች 
                        • የኪነ ጥበብ አስተማሪዎች 
                        • አነስተኛ እና ባህል ላይ የሚያተኩሩ ኪነጥበብ፣ የባህል እና የሰብዓዊነት ድርጅቶች 
                        • መካከለኛ ደረጃ ኪነ ጥበቦች፣ ባህል እና ሰብዓዊነት ለትርፍ ያልተቋቋሙ 
                        • ከፍተኛ ኪነ ጥበቦች፣ ባህል እና ሰብዓዊነት ለትርፍ ያልተቋቋሙ 
                        • ለንድ ለትርፍ የተቋቋሙ የፈጠራ ተቋማት 

                                    ስለ የባህል ዕቅዱ

                                    የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰለሳ-ዓመት አጠቃላይ ዕቅድ፣ የሞንትጎመሪ ማበብ 2050፣ የጸደቀው ኦክቶበር 2022 ዓ.ም ላይ ሲሆን፣ ለካውንቲው አዲስ የባህል ዕቅድ እንዲወጣ ይመክራል። ከ 2 ዓመት በላይ መረጃዎች ከተሰበሰቡ እና አዲስ ዕቅድ እንዲወጣ መሠረቱ ከተደላደለ በኋላ፣ AHCMC የባህል ዕቅድ ማውጣት ሂደቱን እንዲመራ 2024 ዓ.ም ላይ ሜትሪስ አርትስ ኮንሰልቲንግን መርጧል። 

                                    አሁን በዲስቨር (የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ምርምር) ምዕራፍ ላይ፣ አዲሱ የባህል ዕቅድ ነዋሪዎቹ በባህል የበለጸጉ ህይወት እንዲመሩ እና በኪነጥበብ፣ በባህል እና በሰብአዊነት በማህበረሰብ የሚደገፉ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ለመደገፍ ለካውንቲው እና ለመምሪያዎቹ የስነጥበብ እና የሰብአዊነት ባለሙያዎችን፣ የስነጥበብ እና የሰብአዊነት ድርጅቶችን፣ እና በመላው ሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ያሉ የባህል ተቋማትን ለመደገፍ ማዕቀፍ ያቀርባል።

                                    ስለ አማካሪዎቻችን

                                    ሜትሪስ አርትስ ኮንሰልቲንግ ተልዕኮው የባህል ህያውነትን ማሻሻል እና መለካት ሲሆን የምርምራ እና የዕቅድ አውጪ አማካሪ ድርጅት ነው። ሜትሪስ ባህል የሰዎችን ሕይወት ማበልጸግ ላይ ኋይል እንዳለው፣ ማህበረሰቦች እንዲያብቡ እንደሚረዳ፣ ማህበረሰቦችን እንደሚያጠናክር እና አባልነትን ማነሳሳት እንደሚችል ያምናል። በፈጠራ የተሞላ ቦታ የመፍጠር አለም ውስጥ ያለው ስራ ተግባሩን እንዲፈጽም አነሳስቶታል። 2010 ዓ.ም ላይ ለናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዘ አርትስ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚቀርበውን ሪፖርት የእኛ መስራች በጋራ ደርሷል። ሜትሪስ ለማህበረሰብ ዕድገት ስነ ጥበባት እና ባህል ወሳኝ መሳሪያ ሊሆኑ እንደሚችሉ መለየት ላይ ዋና ተሟጋች እንደሆነ ይቀጥላል። ወሳኝ የሆኑ አገልግሎቶችን ይሰጣል እነዚህም- የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ማህበረሰብ እና የስነጥበባት ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች እና የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን የሚጨምሩ በመላው ካውንቲ ውስጥ ለሚገኙ ደንበኞች የማቀድ፣ ፕሮግራም ማውጣት፣ ግምገማ፣ እና ለመስክ ግንባታ ጥናት ማድረግ ናቸው። 

                                    የባህል ዕቅድ ማውጣት ምንድን ነው እና ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ምን ሊፈይድ ይችላል?

                                    የባህል ዕቅድ ማውጣት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችን የሚለይ፣ መዋዕለ ንዋዮችን የሚመራ፣ ስለ ስነጥበብ እና ባህል በተመለከተ ለአካባቢው ፖሊሲዎች ማሳወቅ ስራ የሚሰሩ በቦታ ላይ የተመሰረቱ ዕቅዶችን የመፍጠር ተግባር ነው። የባህል ዕቅዶች አንድ አካባቢ (በዚህ ጉዳይ ላይ ሞንትጎመሪ ካውንቲ) የሚከተሉትን እንዴት እንደሚያከናውን እገዛ ይሰጣሉ፦

                                    • የመንግስት እና የግል ዘርፍ ገንዘቦችን መጠቀም 
                                    • ተቋማትን መገንባት 
                                    • ደንቦችን ማውጣት ወይም መቀየር 
                                    • የህዝብ ቦታዎችን እና የመንግስት ህንፃዎችን መጠቀም 
                                    • የኢኮኖሚ ልማት እና ቱሪዝምን ማበረታታት 
                                    • የትምህርት ወይም የስነ ጥበብ ፕሮግራሞችን መደገፍ 
                                    • በካውንቲው ውስጥ ስነ ጥበባትን እና ባህልን የሚነኩ ሌሎች ውሳኔዎችን መወሰን 

                                                እንደዚህ ያሉ ጉዳዮች ላይ ካውንቲው እንዴት እንደሚወስን በመግራት፣ የባህል ዕቅዶች በተጨማሪም የካውንቲውን የገንዘብ ምንጭ እና ፖሊሲ ውሳኔዎች ላይ ተጽእኖ ያደርጋል። ለሁሉም ነዋሪዎች የስነጥበባት እና የባህል ፕሮግራሞች ላይ ፍትሃዊ የሆነ ተደራሽነት እንዲኖር ያበረታታል። የመኖሪያ ቤት፣ የኢኮኖሚ ልማት፣ የጤና እና የትምህርት ጉዳዮች ላይ ካውንቲው የሚያደርገው ጥረት ላይ ፈጠራን በማከል እና አዳዲስ አመለካከትን በማምጣት ባህላዊ ባልሆነ መንገድ የመንግስት ስራ ላይ እንዴት ስነ ጥበባት፣ ባህል እና ሰብዓዊነት ሊዛመዱ እንደሚችሉ ፍኖተ ካርታዎችን ያወጣል። የባህል ዕቅዶች፣ ልክ እንደ ባለቤትነት የባህል ልማት ዕቅድ በተጨማሪም በአካባቢው የሚገኙ ቦታዎች የባህል እና የዘር ፍትሃዊነትን እንዲያሳድጉ እና የጸረ-ዘረኝነትን ፖሊሲዎች ማራመድ እንዲችሉ መሰረቱን ይገነባል።

                                                አሁን ማቀድ ለምን አስፈለገ?

                                                የሞንትጎመሪ ካውንቲ የመጨረሻው የባህል ዕቅድ የወጣው 2002 ዓ.ም ላይ ነበር። ከዚያን ጊዜ አንስቶ፦

                                                • ሞንትጎመሪ ካውንቲ በፍጥነት አድጓል እና በጣም ብዝማነትን ጨምሯል። ከ 2000 እስከ 2020 ዓመት ድረስ የካውንቲው የህዝብ ቁጥር መጠን 20 በመቶ ጨምሯል። በተጨማሪም፣ በዚህ ተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ የካውንቲው ነጭ ያልሆኑ ነዋሪዎች ቁጥር በ 80 በመቶ ጨምሯል። በአሁኑ ሰዓት በግምት 60 ከመቶ የሚሆነው ህዝብ ነጭ ያልሆነ ነው። 
                                                • ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሁላችንም ላይ ተጽእኖ አሳድሯል፣ ከወረርሽኙ እና ከስራ መዘጋቱ ድረስ ያለው ሰፊው የምጣኔ ሀብት እና የማህበራዊ ለውጦች በተጨማሪ፣ አርቲስቶች እና ስነ ጥበቦች እና የባህል ድርጅቶች የገቢ ማጣት ሁኔታ ታይቶባቸዋል እና ፕሮጀክታቸውን እና ፕሮግራማቸውን እንዴት እንደሚያስቀጥሉ እና ደንበኞቻቸውን እና ማህበረሰቦቻቸውን እንደሚያገልግሉ ለውጦችን እንዲያደርጉ ተገደዋል። 
                                                • የእኛ ተልዕኮዎች እና እሴቶች እየተሻሻሉ መጥተዋል። ሁለቱም  AHCMC እና ካውንቲ ካውንስሉ የገንዘብ ማውጣት፣ ፕሮግራም መቅረጽ እና ውሳኔ መስጠት ላይ የዘር ፍትሃዊነትን ለማስረጽ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል። 
                                                • የባህል ዕቅድ ማውጣት ሥነምግባር በራሱ ለውጥ አሳይቷል። የተለመደው የባህል ዕቅድ ማውጣት ስራ አርቲስቶችን እና የባህል ተቋማትን ማገልገል እና ከስነ ጥበቦች እና ከባህል እንቅስቃሴዎች ላይ የሥነ ምጣኔ ጥቅሞችን ማግኘት ላይ ያተኩራል። እነዚህ አስተሳሰቦች አሁንም ቢሆን ለጥረቱ ማዕከላዊ በመሆን ያገለግላሉ፣ ነገር ግን የባህል ዕቅድ ትኩረት ዛሬ በበጣም ሰፊ ነው። ዘመናዊ የባህል ዕቅድ ማውጣት ሂደት ስነ ጥበብ እና ባህል እንዴት እንደሚቆራኙ እና የካውንቲውን ሌላኛውን ስራ እና ልክ እንደ መኖሪያ ቤት፣ ጤና፣ እና ደህንነት እና የማህበረሰብ ግንባታ የመሳሰሉ፣ ወሳኝ የነዋሪዎችን ህይወት ገጽታዎችን ሊያራምዱ  ይችላሉ። 
                                                • ካውንቲው ስነ ጥበብ እና ባህል ላይ መዋዕለ ንዋይ እያፈሰሰ ያለ ሲሆን ይሄም ዊተን አርትስ ኤንድ ካልቸራል ሴንተር ዕቅድ ማውጣት ያካትታል። ይሄ ፕሮጀክት ስነ ጥበብ እና ባህል ላይ ከካውንቲው በተለምዶ ድጋፍ ላላገኙ ማህበረሰቦች እና ድርጅቶች መዋዕለ ንዋይ ድጋፍ ለመስጠት ዕድሉን ይከፍታል። 

                                                          ስነ ጥበብ እና ባህል የእኛ ራስን የመግለጽ፣ ጤናችንን ለማህበረሰባችን እና እርስ በእርስ አባላት መሆናቸንን ወሳኝ አካል መሆናቸውን እንገነዘባለን። ስነ ጥበቡ የሁሉም ሰው እንደሆነ እና እያንዳንዱ ቀን ላይ ባህል ደግሞ በዙሪያችን አለ። ለካውንቲው አዲስ የባህል ዕቅድ የማውጣት ሂደት ላይ፣ ለሁሉም ነዋሪዎች የስነ ጥበብ እና የባህል ተሞክሮ እና ራስን የመግለጽ ተደራሽነት የሚያሳድግ መዋቅር ውስጥ የእኛን የዘመኑ ዕውቀቶች፣ መርሆች፣ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮችን በጋራ ማቀናጀት እንችላለን።

                                                          በዚህ ዕቅድ የማውጣት ሂደት ውስጥ ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

                                                          የባህል ዕቅድ ማውጣት ሂደቱን የሚመራው አቃፊ ጥያቄ፦ 

                                                          የሞንትጎመሪ ካውንቲ ነዋሪዎቹ በባህል የበለጸጉ ህይወቶችን እንዲመሩ እና በማህበረሰብ የሚደገፉ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በኪነጥበብ፣ በባህል እና በሰብአዊነት እንዴት መርዳት ይችላል? 

                                                          ከAHCMC አመራር ጋር፣ ሞንትጎመሪ ካውንቲ የባህላዊ ዕቅዱን መሠረት መጣል ሲጀምር ከሁለት ዓመት በላይ ሆኖታል። እንደ የባህል ንብረት ካርታ ፕሮጀክት፣ በሥነ ጥበባት እና በባህል ላይ አንጸባራቂ ንግግሮች እና መድረኩን ማዘጋጀት ከመሳሰሉት ጥረቶች ሞንትጎመሪ ካውንቲ ለዚህ የባህል እቅድ ጥረት በማህበረሰብ የሚደገፉ እሴቶችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች በመለየት ትልቅ እመርታን ምጥቷል። በዚህ ስራ ላይ በመመስረት የባህል እቅዳችን ምርምር እና የማህበረሰብ ተሳትፎን ይዳስሳል፦ የባለቤትነት ስሜት፣ የባህል ዘርፍ መካችነት እና መስተጋብር። 

                                                          ባለቤትነት፦ ሁሉም ሰው ባለቤትነት የሚሰማው እና በባህል የበለጸገ ህይወት መምራት የሚችል ማህበረሰብ መፍጠር 

                                                          ቁልፍ ጥያቄዎች፡- የጥበብ፣ የባህል እና የሰብአዊነት መዋዕለ ንዋዮች እና ፖሊሲዎች ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፈጣን እና የተለያየ የህዝብ ቁጥር እድገት ምላሽ መስጠት እና ለሁሉም ነዋሪዎች የኪነጥበብ እና የባህል ሀብቶች ተደራሽነትን ማስፋት እና የዘር እኩልነትን ማሳደግ የሚችሉት እንዴት ነው? 

                                                          የባህል ዘርፍ መካችነት፦ አርቲስቶቻችን እና የባህል ማህበረሰቦቻችን እንዲያድጉ መርዳት 

                                                          ቁልፍ ጥያቄዎች፡- የካውንቲው የኪነጥበብ እና የባህል መዋዕለ ንዋዮች እና ፖሊሲዎች አቅምን ለማጠናከር፣ መዋቅራዊ ክፍተቶችን ለመፍታት እና ለቀጣይ ወረርሽኙ ተፅእኖዎች እና ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት እና የመንግስት ፖሊሲ ተግዳሮቶች የኪነጥበብ፣ የባህል እና የሰብአዊነት ዘርፍን በተሻለ ሁኔታ እንዴት ሊደግፉ ይችላሉ? 

                                                          ተቆራኝነት፦ የማህበረሰብ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ጥበብን፣ ባህልን እና ሰብአዊነትን መጠቀም  

                                                          ቁልፍ ጥያቄዎች፡- እንደ መኖሪያ ቤት፣ ኢኮኖሚ ልማት፣ ደህንነት/ጤና፣ ትምህርት፣ የማህበረሰብ ግንባታ እና የአካባቢ አስተዳዳሪነት ባሉ ጉዳዮች ላይ ካውንቲው አዲስ መንገድ እሴት ለመጨመር የሚያደርገው ጥረቶች ላይ ጥበብ፣ ባህል እና ሰብአዊነት ከመንግስት እና ከአካባቢው መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (NGOዎች) ሥራ ጋር እንዴት ሊገናኙ ይችላሉ?

                                                          ምን ለመጠበቅ ይችላሉ?

                                                          የካውንቲውን የባህል ዕቅድ ማውጣት ሂደትን እንዲመራ AHCMC ከ ሜትሪስ አርትስ ኮንሰልቲንግ ጋር በጋራ ይሰራል። ሜትሪስ ስራውን የጀመረው ሴፕቴምበር 2024 ሲሆን ለነዋሪዎች፣ ስነ ጥበበኞች እና የባህል ክዋኞች፣ ለስነጥበብ፣ የባህል እና የሰብዓዊነት ድርጅቶች፣ ለካውንቲው መንግስት ኤጀንሲዎች፣ እና ሌሎች ጠቃሚ ድምጾች የመድረስ ተግባራትን ይፈጽማል። ሜትሪስ በመላው 2025 ዓ.ም ላይ የተሳትፎ እና የዕውቀት መሰብሰብ እንቅስቃሴዎችን ይፈጽማል እና በሰበሰቡት የብዝሐነት የማህበረሰብ ግብዓቶች በኩል የሚቃኙ ፍትሃዊ፣ አካታች እና መጪውን የሚያዩ ዕቅዶችን ይፈጥራል በፌብሩዋሪ 2026 ዓ.ም ላይ፣ ከ Thrive 2050 አጠቃላይ ዕቅድ ጋር አብሮ ለመስራት በካውንቲው ካውንስል፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፕላኒንግ፣ በM-NCPPC እና በAHCMC ቦርድ በኩል እንዲተገበር እንፈልጋለን። የAHCMC ሰራተኞች እና ቦርዱ፣ ከተለያዩ የካውንቲው መመሪያ የተውጣጡ የአማካሪ ኮሚቴ፣ እና የሰፊው ማህበረሰብ አማካሪ ቡድኖች የዕቅድ ማውጣት ሂደቱ ላይ ከሜትሪስ ጋር በጋራ ይሰራሉ።

                                                          ሂደቱ ሲቀጥል ጊዜ የተሳትፎ ዕድሎች ማግኘት ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይሄንን ድረገጽ ይጎብኙ።